Babel

The Tower of Babel (Genesis 11: 1-9)

አማርኛ (Amharic)

  1. ፤ ምድርም ሁሉ በአንድ ቋንቋና በአንድ ንግግር ነበረች።
  2. ፤ ከምሥራቅም ተነሥተው በሄዱ ጊዜ በሰናዖር ምድር አንድ ሜዳ አገኙ፤ በዚያም ተቀመጡ።
  3. ፤ እርስ በርሳቸውም። ኑ፥ ጡብ እንሥራ፥ በእሳትም እንተኵሰው ተባባሉ። ጡቡም እንደ ድንጋይ ሆነላቸው፤ የምድርም ዝፋት እንደ ጭቃ ሆነችላቸው።
  4. ፤ እንዲህም። ኑ ለእኛ ከተማና ራሱ ወደ ሰማይ የሚደርስ ግንብ እንሥራ፤ በምድር ላይ ሳንበተንም ስማችንን እናስጠራው አሉ።
  5. ፤ እግዚአብሔርም የአዳም ልጆች የሠሩትን ከተማና ግንብ ለማየት ወረደ።
  6. ፤ እግዚአብሔርም አለ። እነሆ፥ እነርሱ አንድ ወገን ናቸው፥ ለሁሉም አንድ ቋንቋ አላቸው፤ ይህንም ለማድረግ ጀመሩ፤ አሁንም ያሰቡትን ሁሉ ለመሥራት አይከለከሉም።
  7. ፤ ኑ፥ እንውረድ፤ አንዱ የአንዱን ነገር እንዳይሰማው ቋንቋቸውን በዚያ እንደባልቀው።
  8. ፤ እግዚአብሔርም ከዚያ በምድር ሁሉ ላይ በተናቸው፤ ከተማይቱንም መሥራት ተዉ።
  9. ፤ ስለዚህም ስምዋ ባቢሎን ተባለ፥ እግዚአብሔር በዚያ የምድርን ቋንቋ ሁሉ ደባልቋልና፤ ከዚያም እግዚአብሔር በምድር ሁሉ ላይ እነርሱን በትኖአቸዋል።

You can also see the above text as an image if it doesn't display correctly in your browser.

Information about the Amharic language and the Ge'ez script
Amharic language learning materials

Tower of Babel in related languages

Amharic, Arabic, Aramaic, Hausa, Hebrew, Maltese, Syriac, Tamasheq, Tigrinya

Tower of Babel in other languages

> Mercure Luna Hotel
> Noria Resort Sharm El Sheikh
> Novotel Sharm El Sheikh Hotel
> Partner Turquoise Hotel
Sharm El Sheikh Hotels from DirectRooms

Support this site - make a donation